የባለአክሲዮኖች 16ኛ መደበኛ እና 13ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ የስብሰባ ጥሪ
በኢ.ፌ.ድ.ሪ ንግድ ህግ አንቀፅ 366(1)፣ 367(1 እና 2)፣ አንቀፅ 370 አንዲሁም በአክሲዮን ማህበሩ መመስረቻ ፅሁፍ አንቀፅ 13(2) መሠረት የዓባይ ኢንሹራንስ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 16ኛ መደበኛ እና 13ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ህዳር 26 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሠዓት ጀምሮ አዲስ አበባ በሚገኘው ዲ ሊዮፖል ሆቴል ይካሄዳል፡፡ በመሆኑም የተከበራችሁ የማህበሩ ባለአክሲዮኖች በዕለቱ ጉባዔው ላይ እንድትገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡